Quantcast
Channel: Sodere
Viewing all articles
Browse latest Browse all 19

ከአያት –ጦር ሃይሎች ያለው የባቡር መስመር ዛሬ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል Addis light rail’s Ayat-Tor Hayloch route starts to give service

$
0
0

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት፣ 29፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ የምስራቅ ምእራብ የባቡር መስመር የሆነው ከአያት አደባባይ – መገናኛ – ጦር ሃይሎች የሚዘልቀው የባቡር መስመር ዛሬ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

አገልግሎቱም ዛሬ በጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሯል።

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ደረጀ ተፈራ አገልግሎቱ በቀን ለ16 ሰዓታት እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

የአገልግሎት ክፍያ ታሪፉም ከቃሊቲ ዳግማዊ ሚኒሊክ ካለው መስመር ጋር ተመሳሳይ መሆኑንም አቶ ደረጀ ገልጸዋል።

ታሪፎቹም እንደየርቀቱ 2 ብር፣ 4 ብር እና 6 ብር መሆናቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪም ከ35 የቲኬት መሸጫ ቢሮዎች ትኬት በመግዛት አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

በመስመሩ እንደ ተጠቃሚው ብዛት ከ20 እስከ 21 ባቡሮች ለስምሪት እንደሚውሉም ታውቋል።

መስከረም 9 ቀን 2008 ዓ.ም የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የሰሜን ደቡብ ከፒያሳ ጊዮርጊስ እስከ ቃሊቲ ያለው መስመር በከፊል ስራ መጀመሩ ይታወቃል።

የትራንስፖርት አገልግሎት በተጀመረ ጊዜም በቀን በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ተሳፋሪዎችን እያጓጓዘ በየቀኑ በአማካይ እስከ 200 ሺህ ብር ገቢ እየተገኘ መሆኑም በጊዜው ተነግሯል።

የአዲስ አበበባ የቀላል ባቡር መስመር ግንባታ 32 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው።

39 ጣቢያዎች የተገነቡለትም ሲሆን፥ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያማከለ አገልግሎት ለመሰጠት 12 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መወጣጫዎች እና 22 ሊፍቶች ተገጥመውለታል።

የባቡር ፕሮጀክቱ 474 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የተደረገበት ሲሆን፥ 85 በመቶ ወጪው የተሸፈነው ከቻይና ኤግዚም ባንክ በተገኘ ብድር ነው።

በዳዊት መስፍን

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 19

Trending Articles